Gobezoch

Help · እገዛ

Short answers to the questions students ask most. Still stuck? Write to us: a person answers.
ተማሪዎች በብዛት ለሚጠይቋቸው ጥያቄዎች አጭር መልሶች። አሁንም ካልተፈታልዎ ይጻፉልን፤ መልስ የሚሰጥዎት ሰው ነው።

How do I pay for Plus?ለ Plus እንዴት እከፍላለሁ?

Open gobezoch.com, tap "Get Plus", and pay 299 Birr with telebirr or M-Pesa. Your phone asks for your mobile-money PIN to approve it. Plus opens right away, for 12 months, on the Telegram account you signed in with.

gobezoch.com ይክፈቱ፣ "Get Plus"ን ይንኩ እና 299 ብር በ telebirr ወይም በ M-Pesa ይክፈሉ። ክፍያውን ለማጽደቅ ስልክዎ የሞባይል ገንዘብ የይለፍ ቁጥርዎን (PIN) ይጠይቅዎታል። Plus ወዲያውኑ ለ12 ወራት ይከፈታል፤ የሚከፈተውም በገቡበት የቴሌግራም አካውንት ላይ ነው።

Can a parent pay for me?ወላጅ ሊከፍልልኝ ይችላል?

Yes. In "Get Plus", tap "Ask a parent to pay" and send the link to your parent. They pay from their own phone, and Plus opens on your account.

አዎ። በ "Get Plus" ውስጥ "Ask a parent to pay"ን ይንኩ እና ሊንኩን ለወላጅዎ ይላኩ። ወላጅዎ ከራሳቸው ስልክ ይከፍላሉ፤ Plus በእርስዎ አካውንት ላይ ይከፈታል።

How does the free trial work?የነፃ ሙከራው እንዴት ይሠራል?

Plus is free for 1 day, once per Telegram account and once per phone. Sign in with Telegram, then tap "Try Plus free for 1 day". No payment and no card. When it ends, everything free stays free.

Plus ለ1 ቀን ነፃ ነው፤ ለአንድ የቴሌግራም አካውንት እና ለአንድ ስልክ አንድ ጊዜ ብቻ። በቴሌግራም ይግቡ፣ ከዚያ "Try Plus free for 1 day"ን ይንኩ። ክፍያም ሆነ ካርድ አያስፈልግም። ሙከራው ሲያበቃ በነፃ የነበረው ሁሉ በነፃ ይቀጥላል።

Why do I sign in with Telegram?ለምን በቴሌግራም እገባለሁ?

So your Plus and your progress belong to you, not to one phone. Your account is open on one phone at a time: when you sign in on a new phone, the old one is signed out. Your progress is the same on the website, in Telegram and in the Android app.

Plus እና እድገትዎ የአንድ ስልክ ሳይሆን የእርስዎ እንዲሆን ነው። አካውንትዎ በአንድ ጊዜ በአንድ ስልክ ላይ ብቻ ክፍት ይሆናል፤ በአዲስ ስልክ ሲገቡ በቀድሞው ስልክ ላይ ከአካውንትዎ ይወጣሉ። እድገትዎ በድረ ገጹ፣ በቴሌግራም እና በ Android መተግበሪያ ላይ አንድ ዓይነት ነው።

I have a Plus code from my school or a friend.ከትምህርት ቤቴ ወይም ከጓደኛዬ የተሰጠኝ የ Plus ኮድ አለኝ።

Tap "Get Plus" and type the code under "Have a code". One code is for one student.

"Get Plus"ን ይንኩ እና ኮዱን "Have a code" ስር ይጻፉ። አንድ ኮድ ለአንድ ተማሪ ብቻ ነው።

What can the Telegram bot do?የቴሌግራም ቦቱ ምን ማድረግ ይችላል?

Send /daily for one past national exam question every evening at 7 PM, /top for the weekly leaderboard, /school to set your school, and /parent for a weekly report to your parent.

በየምሽቱ 1:00 ሰዓት አንድ የቀድሞ ብሔራዊ ፈተና ጥያቄ ለማግኘት /daily ይላኩ፤ ሳምንታዊውን የደረጃ ሰንጠረዥ ለማየት /top፣ ትምህርት ቤትዎን ለማስገባት /school፣ ለወላጅዎ ሳምንታዊ ሪፖርት እንዲደርስ ደግሞ /parent ይላኩ።

Can I get my money back?ገንዘቤን መመለስ እችላለሁ?

If Plus did not switch on after you paid, or you were charged twice, we switch it on or refund you. See the payments and refunds page.

ከከፈሉ በኋላ Plus ካልበራ ወይም ሁለት ጊዜ ከተቆረጠብዎ Plusን እናበራለን ወይም ገንዘብዎን እንመልሳለን። የክፍያና ገንዘብ መመለሻ ገጹን ይመልከቱ።

Payments and refunds

How do I reach a person?ሰው ማግኘት የምችለው እንዴት ነው?

Write to @gobezoch_et_bot on Telegram: a team member answers in the same chat, usually within a few hours, between 8:00 and 22:00 Ethiopian time. You can also email support@gobezoch.com.

በቴሌግራም ለ @gobezoch_et_bot ይጻፉ፤ የቡድናችን አባል በዚያው ውይይት ውስጥ ይመልስልዎታል፤ ብዙውን ጊዜ በጥቂት ሰዓታት ውስጥ፣ ከጠዋቱ 2 ሰዓት እስከ ምሽቱ 4 ሰዓት (በኢትዮጵያ ሰዓት) ባለው ጊዜ። በ support@gobezoch.com በኩል በኢሜይል መጻፍም ይችላሉ።

📞 Parents, and anyone with a payment problem, can also call us: +251 95 328 3277

📞 ወላጆች እና የክፍያ ችግር ያጋጠማቸው ማንኛውም ሰው በስልክ ሊደውሉልን ይችላሉ፦ +251 95 328 3277